አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ በትግራይ መዳረስ ለኢትዮጵያ የሰላም ጉዞ የመጀመሪያ እርምጃ ነው

የተለጠፈው በ 07/05/2013 የኤችአር / ቪፒ ብሎግ – በትግራይ ክልል ውስጥ የተነሳው ግጭት ከሁለት ወራት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ሁኔታው ለአካባቢው ህዝብ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ከመሆኑም በላይ በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ክልል ያሉ ሁኔታዎችን እጅግ ተለዋዋጭ አድርጓቸዋል፡፡ እኔም ለኢትዮጵያ አመራር ግልፅ መልእክት አስተላልፌያለሁ ፤ እኛ ለመርዳት ዝግጁ ነን ፣ ነገር ግን ለሰብአዊ ዕርዳታ ሰጪዎች ተደራሽ መንገድ እስካልተገኘ ድረስ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት ያቀደውን የበጀት ድጋፍ መስጠት አይችልም ፡፡

የትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት እንደሚያስታውሰን ሆን ተብለው ግጭቶችን ለማብረድ እርምጃዎች ካልተወሰዱ ግጭቶች እየተባባሱ ይሄዳሉ፡፡ ከሁለት ወራት በፊት የውስጥ ጉዳይ ተብሎ የተጀመረው ጠብ ከክልልሉ እና ፌዴራል መንግሥቱ አልፎ መላውን ቀጠና እያናጋ ይገኛል፡፡ በመሬቱ ላይ ያለው ሁኔታ ግን ፍፁም ከውስጣዊ ‹የሕግ ማስከበር ዘመቻ› ያለፈ ነው፡፡ በዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፣ ግድያ ፣ ከፍተኛ ዘረፋ ፣ አስገድዶ መደፈር ፣ ስደተኞችን በኃይል መመለስ እና ሌሎች የጦር ወንጀሎች ሊሆኑ የሚችሉ ተግባሮች እየተፈፀሙ እንዳሉ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን እየደረሱን ነው፡፡ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከአካባብያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ሰዎች በጣም ርዳታ በሚፈልጉበት ጊዜ ላይ ቢሆኑም በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ተደራሽነት እጅግ ውስን ነው ፣ ይህም የሰብዓዊ ዕርዳታን ለማድረስ በጣም ከባድ ያደርገዋል ፡፡
በመሬቱ ላይ ያለው ሁኔታ ግን ፍፁም ከውስጣዊ ‹የሕግ ማስከበር ዘመቻ› ያለፈ ነው፡፡ በዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፣ ግድያ ፣ ከፍተኛ ዘረፋ ፣ አስገድዶ መደፈር ፣ ስደተኞችን በኃይል መመለስ እና ሌሎች የጦር ወንጀሎች ሊሆኑ የሚችሉ ተግባሮች እየተፈፀሙ እንዳሉ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን እየደረሱን ነው፡፡ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከአካባብያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ሰዎች በጣም ርዳታ በሚፈልጉበት ጊዜ ላይ ቢሆኑም በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ተደራሽነት እጅግ ውስን ነው ፣ ይህም የሰብዓዊ ዕርዳታን ለማድረስ በጣም ከባድ ያደርገዋል ፡፡ በተጨማሪም የግጭቱ መከሰት ለቀጠናውም ተርፏል፣ ለምሳሌ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ ሲሆን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ ወጥተዋል፡፡ 55,000 የሚሆኑ ስደተኞችም ወደ ሱዳን ተሰደዋል፡፡ በሱዳን እና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎችም አደገኛ ፍጥጫዎች እየተባባሱ ነው፡፡ ግጭቱ ሌሎች አገሮችን በማሳተፍ ወይንም ተጽዕኖ በመፍጠር ለአካባቢው መረጋጋት ሁሉ ቀጥተኛ ስጋት ሆኗል፡፡